You are currently viewing የጡት ካንሰር ህክምና አማራጮቹ ምንድናቸዉ?

የጡት ካንሰር ህክምና አማራጮቹ ምንድናቸዉ?

አንዲት ሴት የጡት ካንሰር እንዳለባት ከተረጋገጠ ከሃኪሙ ጋር ስለ ህክምና አማራጮቹ በመነጋገር በጊዜ ወደ ህክምና መግባቱ የተሻለ ሃሳብ ነዉ። በጊዜ እርምጃ መዉሰዱ ደግሞ የካንሰሩን ዳግም መከሰትም ሆነ ወደ ሌላ የሰዉነት ክፍሎች የመሰራጨት ዕድሉን ለመቀነስ ይረዳል። ህክምናዉም በተወሰኑ ቀናት ይጀመራል።

የህክምናዉንም አይነት የሚወስነዉ የካንሰሩ መጠን፣ ካንሰሩ ያለበት የጡት ክፍል እና ሌላ ቦታ መሰራጨት ያለመሰራጨቱ፣ የካንሰር ህዋሳቱ ባሕርይን ለማጥናት የተደረገዉ የላብራቶሪ ምርመራ፣ የእድሜ እና ሌሎች የሰዉነት ጤንነትን እና የታማሚዉ ምርጫ ጭምር በማጤን ነዉ።

የህክምና አማራጮቹ በጡት ላይ ብቻ የሚደረጉ (Local) ወይም ሙሉ ሰዉነት ላይ የሚደረጉ (Systemic)(ሲስቴሚክ) ሊሆኑ ይችላሉ። ቀዶ ህክምና እና የጨረር ህክምና በጡት ላይ የሚደረጉ ሲሆን። ከዚህ ጋር በተጨማሪም ወይም እንደ ካንሰሩ ሁኔታ የሚወሰዱ መድሃኒቶች አሉ ይህም ደግሞ Systemic ወይም በመላ ሰዉነት ላይ የሚደረግ ተብሎ ይጠራል። ይህ በመላ ሰዉነት ላይ የተሰራጩትን የካንሰሩን ህዋሳት ለማጥፋት ይጠቅማል። Systemic (ሲስቴሚክ) ህክምና መድሃኒቶች የሆርሞኖች ህክምና ወይም ሌሎች ኬሚካሎች ሊሆኑ ይችላሉ። ከነዚህ በተጨማሪ የተወሰኑ ህዋሳትን ብቻ በመለየት ለማጥቃት የሚያገለግሉ መድሃኒቶችም (Targeted) ህክምና ሊሆን ይችላል።

ቀዶ ህክምና፤ ኬሞቴራፒ፤የጨረር ህክምናና ሌሎች መድሀኒቶች አንድ ላይ (በተለያየ ቀደም ተከተል) ወይም ለየብቻ እንደየ ካንሰሩ እና የታማሚዉ ሁኔታ በመጠቀም ሊታከም ይችላል።
ከህክምናዉ ጋር አብሮ የሚነሳዉ ጥያቄ የካንሰር ህመም ይድናል ወይ የሚለዉ ነዉ።  ካንሰሩ በጊዜ ከታወቀ እና ህክምናዉ ከተጀመረ የመዳን እድሉ ከፍተኛ ነዉ። አሁን ላይ ባለዉ ሁኔታ ከህክምና ባልተናነሰ በየጊዜዉ የሚደረገዉ የልየታ ምርመራ ማካሄዱ እና መከታተሉ የተሻለ ዉጤት ያስገኛል። 
ከስር ባሉት መተግበሪያዎች ለሌሎች እንዲደርስ ሼር በማድረግ መልዕክቱን እናድርስ።

አመሰግናለሁ።
ዶ.ር አብዱ አደም 
የካንሰር ህክምና ረዳት ፕሮፌሰር

This Post Has One Comment

Leave a Reply