የካንሰር ስፔሺያሊስት ሃኪም ማማከር ይፈልጋሉ?

ዶ.ር አብዱ አደም እባላለሁ። በቅዱሰ ጳዉሎስ ሆስፒታል ሚሌኒዬም ህክምና ኮሌጅ የካንሰር ህክምና ረዳት ፕሮፌሰር ነኝ፣  

በአለማችን ሁለተኛ ደረጃ ላይ በገዳይነቱ የተቀመጠዉ እና በሀገራችን በአመት ከ 45 ሺህ በላይ ሰዎች ህልፈት ምክንያት የሆነዉ የካንሰር ህመም መሆኑ፣ እስካሁን በሀገራችን የሚገኙ የካንሰር ህክምና ስፔሺያሊስቶች ከ20 ያነሱ መሆናቸዉን በመገንዘብ ለህብረተሰቡ የግንዛቤ መፍጠሪያ፣ ታካሚዎችና ሌሎች የጤና ባለሙያዎች ካሉበት ሆነዉ ሊያማክሩኝ የሚችሉበት ድረ- ገጽ ነዉ። 

በዚህ ድረ-ገጽ የሚያገኟቸዉ አገልግሎቶች

በሀገራችን የካንሰር ህክምና ስራ ላይ የድርሻዬን አስተዋጽዖ ከማበርከት አንጻር ይህን ድረ ገጽ የካንሰር ስፔሺያሊስት ሃኪም በአቅራቢያቸዉ ማግኘት ያልቻሉ የጤና ባለሙያዎች፣ ታካሚዎች ወይም ሌላዉ የህብረተሰብ ክፍል በሚከተሉት መንገዶች ሊጠቀም ይችላል።

img_854697

የህክምና ክትትል

የካንሰር ታማሚዎች ህክምናቸዉን በካንሰር ህክምና ስፔሺያሊስት ለማድረግ ሃኪሙን ለማግኘት የሚያወጡትን ወጪ እና ልፋት በማስቀረት ታካሚዎች ካሉበት ሆነዉ እንዲያገኙ ማድረግ።

Graphic_Cancer-Patient-Decision-Variables-3

የካንሰር ህክምና ማማከር

ታካሚዎችም ሆነ ሌሎች የጤና ባለሙያዎችን በሀገር ዉስጥም ሆነ በዉጪ ስለሚሰጡ የካንሰር ህክምና አማራጮች ማማከር እና ህክምናዉን ማመቻቸት።

breast-cancer-support-products-dispensaries

የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርቶች

በህብረተሰቡ ዘንድ ስለካንሰር ያለዉን ግንዛቤ የተሻለ እንዲሆን በየጊዜዉ የተለያዩ ትምህርቶችን ማዘጋጀት እና በተለያዩ የድጂታል መተግበሪያዎች በመጠቀም ማስተማር እና የባህሪይ ለዉጥ ማምጣት።

+
የዉጭ ሀገር ህክምና ማማከር
+
ደስተኛ ደምበኞች
+
የግንዛቤ ማስጨበጫ መልዕክቶች የደረሳቸዉ ሰዎች
+
ክትትል ላይ የሚገኙ

ከአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች

አገልግሎቱን ከጀመርኩ በኋላ የተሰጡ አስተያየቶች…

ውድ ዶ.ር አብዱ ህክምናዬን ከጀመርኩበት ጀምሮ ከሀገር ዉጪ ከሚገኙ ሀኪሞች ጋር በመስራት ህይወቴን በማትረፋችሁ እና አሁንም ካለሁብት ሆኜ በድረ ገጽዎ ጤናዬን እየተከታተላችሁ ስላላችሁ አላህ ይስጥልኝ፣ አመሰግናለሁ።
ወ/ሮ ሙሃባ መ.
የዉጭ ሀገር ህክምና ማማከር አገልግሎት ያገኙ ታካሚ
አብዛኛዎቹ የሀገራችን የካንሰር ታማሚዎች ወደ ህክምና የሚመጡት ህመማቸዉ ከጠና በኋላ በመሆኑ ህክምና በጊዜ ባለማግኘታቸዉ እና አስፈላጊዉን ቅድመ ምርመራ ባለማድረጋቸዉ ህክምናቸዉ ላይ የሚያሳድረዉን አሉታዊ ተጽዕኖ ለመቀነስ የጀመርከዉ ስራ እጅጉን የሚበረታታ ነዉ።
ወ/ሮ. ሳምራዊት አ.
የካንሰር ህክምና ባለሙያ
በሀገራችን በዘርፉ የተማሩ ሀኪሞች አንዱ ለ 5.5 ሚሊየን በላይ ህዝብ በሆነበት ሀገራችን የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርቶችን ከጊዜህ በመቆጠብ እያደረስክ ስላለህ ላመሰግን እወዳለሁ፤ በዚሁ ቀጥል።
አቶ ዳዊት ከ.
የካንሰር ትምህርቶች የሚከታተል
ይህ የጀመርከዉ የድረ ገጽ ላይ ማማከር እና ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራ በሀገራችን ሀኪሞች ዘንድ ብዙም ጥቅም ላይ ያልዋለ እና የህብረተስብ ክፍሉን ስለካንሰር ያለዉን ግንዛቤ በመጨመር ረገድ፣ የካንሰር ስፔሺያሊስት ሃኪሞችን ለማግኘት የሚደረገዉን ጊዜ እና ገንዘብ ከመቆጠብ አኳያ እና ታካሚዉና ሃኪሙ መሃል ድልድይ በመሆን የተሻለ ዉጤት እንዲገኝ የሚያስችል ስራ በመሆኑ ላበረታታህ እና በምችለዉ ልደግፍህ ቃል እገባለሁ።
ዶ.ር ተመስገን እ.
ሃኪም፣ UX እና UI ዴቬሎፐር

የቅርብ ጊዜ ጦማሮች

በየጊዜዉ ስለ ካንሰር ከምጽፋቸዉ ጦማሮች መካከል በቀርብ ጊዜ የተጻፉትን እዚህ ጋር ያገኛሉ።