You are currently viewing የጡት ካንሰር እና አጋላጭ ሁኔታዎቹ

የጡት ካንሰር እና አጋላጭ ሁኔታዎቹ

           ጤነኛ ጡት ስዕሉ ላይ እንደሚታየው ወተት የሚያመነጩ እጢዎች (lobes)፤ ቱቦወች (ducts)፤ ስብ (fat)፤ ጡንቻ (muscle) እና ሌሎችንም የያዘ የሰውነታችን ክፍል ነው፡፡

በብት ውስጥ የሚገኙ (ንፊፊት) ሊምፍ ኖድ (Lymph nodes) የሚባሉ የሰውነት በሽታ መከላከያ ሥርዓት አካል የሆኑና ካንሰር ሲከሰትም ወደነሱ በቅድሚያ የሚዛመትባቸው አካላት አሉ ፡፡ የጡት ከንሰር በጡታችን ውስጥ ካሉ ማነኛውም ኖርማል ክፍሎች ሊነሳ ቢችልም ከ95% በላይ የሚሆነው መነሻው ግን ወተት ከሚያመነጩ እጢዎች (lobes) እና ቱቦወች (ducts) ነው፡፡

   አጋላጭ ሁኔታወቹስ ምንድን ናቸው?

👉ሴት ጸታ – ሴቶች ከወንዶች በ 150-200 እጥፍ የበለጠ የመያዝ አድልአላቸው፡፡
👉የእድሜ መጨመር – ብዙ ጊዜ ከ30 አመት በታች አየከሰትም፡፡
👉ሴቶች የወር አበባ የሚያዩበት እድሜ ረጅም መሆን – የወር አበባ በልጅነት መጀመርና ሲቆም (የእርጣት እድሜ) መዘግየት (Early menarche and late menopause)
👉መካንነት
👉የመጀመሪያ ልጅ የተወለደበት እድሜ ከፍ ያለ መሆን (ብዙ ጥናቶች ከ 35 አመት በላይ ይላሉ)
👉ጡት አለማጥባት
👉ውፍረት (በተለይ ደግሞ ቦርጭ)
👉አንድ ጊዜ በጡት ካንሰር መያዝ ለቀሪው ጡት እንደአጋላጭ ይሆናል
👉የቤተሰብ ታሪክ መኖር(በዘር የሚተላለፍ የጡት ካንሰር)
👉ሲጋራ ማጨስ
👉አልኮል መጠጣት ይገኙበታል።
ተባብረን የተሻለ ግንዛቤ ስለጡት ካንሰር እንፍጠር!
አመሰግናለሁ።
ዶ/ር አብዱ አደም
የካንሰር ህክምና ረዳት ፕሮፌሰር

Leave a Reply