You are currently viewing የጡት ካንሰር ምልክቶች እና ማረጋገጫ መንገዶች

የጡት ካንሰር ምልክቶች እና ማረጋገጫ መንገዶች

 

የጡት ካንሰር ምልክቶች ምንድናቸዉ?

👉 በጡት ላይ የሚከሰት እብጠት
👉 ደም የቀላቀለ ፈሳሽ ከጡት መዉጣት
👉 የጡት ቆዳ ወደ ዉስጥ መሰርጎድ
👉 የጡት ወይም የጡት ጫፍ ህመም
👉 የጡት ጫፍ ወደ ዉስጥ መግባት
👉 የጡት ቆዳ ቀለም ወደ ቀይነት ማድላት
👉 የጡት ቆዳ መሻከር (የብርቱካን ቆዳ ልጣጭ ይመስል)
👉 የብብት ንፊፊት መጠን መጨመር ወይም እርስ በርስ መያያዝ
👉 የሁለቱ ጡት መጠን እኩል ያለመሆን እና የታመመዉ ማበጥ … ይገኙበታል።

እነዚህ ምልክቶች አሉ ማለት ሁሌም ካንሰር ነዉ ማለት ሳይሆን በሚኖሩበት ጊዜ በትክክል መታየቱ እንደ-አብዛኞቹ ሰዎች ህመሙ ከጠና በኋላ ለመፍትሄ ከመቸገር ያግዘናል።

✍️ የጡት ካንሰር መሆኑ በምን ይረጋገጣል?

የህመሙ መኖር የሚታወቀው መጀመሪያ ከላይ ባሉት ምልከቶች ሲሆን ነገር ግን ሌሎች ካንሰር ያልሆኑ ህመሞችም ተመሳሳይ ምልክቶችን ሊያሳዩ ስለሚችሉ ካንሰር ስለመሆኑ በትክክል በሚከተሉት ምርመራወች መረጋገጥ አለበት፡፡

👉የናሙና ምርመራ (ባዮፕሲ ወይም በመርፌ የሚወሰድ ናሙና)
👉ደረጃውን ለማወቅ ደግሞ ራጅ፤ አልትራሳውንድ እና ሌሎችም እንደ አስፈላጊነቱ መሰራት አለባቸው፡፡
አመሰግናለሁ።
ዶ.ር አብዱ አደም
ረዳት ፕሮፌሰር እና የካንሰር ህክምና ስፔሺያሊስት

 

This Post Has One Comment

  1. ELILITA ALEMU

    ዶ/ር!
    ሰላም ሰላም!
    አንድ ጥያቄ ልጠይቆት!
    በጡት ጫፍ ላይ ምንም ሕመምም ሆነ እብጠት ሰይኖር ነገር ጠጠር ነገር ብቻ ከታየ የጡት ካንሰር ነው ማለት ይቻላል?

    አመሰግናለሁ።

Leave a Reply