You are currently viewing ካንሰር ምንድነዉ?

ካንሰር ምንድነዉ?

                          ሰውነታችን በትሪሊየን ከሚቆጠሩ ሴሎች የተገነባ ነው፡፡ ከጥቂቶች በስተቀርም እነዚህ ሴሎች እጅግ በተቀናጀና ስህተት አልባ በሆነ መልኩየሴል ሳይክልተብሎ በሚጠራ የመራባት ሂደት ውስጥ ያልፋሉ፡፡ ይህን የሴል ሳይክል የሚቆጣጠሩ የፍተሻ ዘረመሎች (genetic check points) እና ካንሰር እንዳያድግ የሚያደርጉ ዘረመሎች (tumor suppressor genes) ሲሆኑ፡ በነዚህ ዘረመሎች ላይ በማንኛውም ምክንያት የሚደርስ ጉዳት ሴሎች ከቁጥጥር ውጭ በሆነና ሰውነታችን ሊቋቋመው በማይችለው ደረጃ እንዲባዙ ያደርጋል፡፡ በዚህ ምክንያት የሚከሰተው በሽታም ካንሰር ተብሎ ይጠራል፡፡ ካንሰ አንድ ህመም ሳይሆን ማንኛውንም የሰውነታችን ክፍል ሊያጠቃ የሚችልና 100 በላይ ለሚሆኑና ከላይ በጠቀስነው ምክንያት ለሚከሰቱ ህመሞች የተሰጠ መጠሪያ ነው፡፡ የካንሰር ሴሎች ቁጥራቸው ሲጨምርና በመጠንም ሲያድጉ የተነሱበትን አካል፣ አጠገቡ የሚገኙ አካላትንና በመጨረሻም ሩቅ ያሉ የሰውነት ክፍሎቻችን ላይ ጉዳት በማድረስ ለሞት ይዳርጋሉ፡፡
አመሰግናለሁ።
. አብዱ አደም
የካንሰር ህክምና እና ረዳት ፕሮፌሰር

Leave a Reply