You are currently viewing ራሴን ከጡት ካንሰር እንዴት መጠበቅ እችላለሁ?

ራሴን ከጡት ካንሰር እንዴት መጠበቅ እችላለሁ?

  • በተቻለ መጠን ለጡት ካንሰር አጋላጭ የሆኑ ምክንቶችን በማስወግድ እና የጡት ካንሰር ቅድመ ምርመራ በየጊዜዉ በማድረግ እና ህመሙ ሳይጠና በመታከም በካንሰሩ ምክንያት ከሚመጣዉ ጉዳት ራስን መጠበቅ ይቻላል።

የጡት ካንሰር የቅድም ካንሰር ምርመራ ካላቸው ካንሰሮች አንዱና ቀዳሚው ሲሆን ያደጉት ሀገራትም በጡት ካንሰር ምክንያት የሚከሰተውን ሞት በጣም ለመቀነስ የተጠቀሙበት ዋነኛው መንገድ ነው፡፡ የቅደመ ካንሰር ምርመራ አላማውም ካንሰሩ ሳይከሰት ወይም መዳን በሚችልበት ደረጃ ላይ እያለ ለማወቅ ነው፡፡ በተለያዩ አለም አቀፍ ድርጅቶች አሰራር መሰረትም የጡት ካንሰር ቅደመ ምርመራ እንደሚከተለው መደረግ አለበት፡፡
ሁሉም ሴቶች በራሳቸው ጡታቸውን ምርመራ ማድረግ ይኖርባቸዋል። ይንንም ጊዜና ቦታ ሳይገድባቸው (ለምሳሌ ልብስ ሲቀይሩ፤ ሻወር ሲወስዱ፤ሲተኙ፤ መስታዎት ሲያዩ) ማድረግ የሚኖርባቸውና የምንጊዜም ተግባራቸው ሊሆን ይገባል፡፡

በቋሚነት መደረግ ያለባቸዉ ምርመራዎች በዕድሜ ሲከፈሉ፡

  • 20 እስከ 39 ዓመት በየወሩ በራስ የሚደረግ ምርመራ እና በየ ሶስት አመቱ በሃኪም የሚደረግ ምርመራ
  • 40 እስከ 49 ዓመት፡በየወሩ በራስ የሚደረግ ምርመራ እና በየዓመቱ በሃኪም የሚደረግ ምርመራ እና የመጀመሪያዉን ማሞግራፊ ምርመራ ማድረግ እና በየሁለት አመቱ መታየት
  • 50 ዓመት እና ከዚያ በላይ፡በየወሩ በራስ የሚደረግ ምርመራ እና በየ አመቱ በሃኪም የሚደረግ ምርመራ እና ማሞግራፊ በየአመቱ ማድረግ እንደ አለም ጤና ጥበቃ መረጃ መሰረት ይገባቸዋል።
    ለሌሎችም እንዲደርስ ከስር በተቀመጡ መተግበሪያዎች ሼር ያድርጉ።
    አመሰግናለሁ።
    . አብዱ አደም
    የካንሰር ህክምና ረዳት ፕሮፌሰር

Leave a Reply